በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የሜሪላንድ ደብረ ብሥራት ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሰኔ 19/2011 ዓ/ም ወይም JUNE 2018 በልዑል እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በሜሪላንድ ሲልቨር ሰፕሪንግ ተቋቋመ።
ቤተክርስቲኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን እምነት፤ ዶግማ፤ ቀኖናንና ትውፊትን የሚከተል ሲሆን፤ ቤተክርስቲያን የተቋቋመበት ዋና አላማ የእግዚአብሔርን የመንግሥቱን ወንጌል ለማስፋፋት ለምእመናንና ምእመናት በአቅራቢያቸው መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግና ለልጆች ኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ አስተዳድግና ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በተጠናከረ መልኩ ማስተማር ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣውን የአበው ሃይማኖትን ተከትሎ ተገቢውን መንፈሳዊ አገልግሎት ለምዕመናን መስጠት ነው።በአስተዳደራዊ ሁኔታዎች ደግሞ ያለንበት ሀገር የኑሮና የአሠራር ሁኔታዎችን ያገናዘበ ፤የሜሪላንድ እስቴት የሃይማኖት ድርጅት ማቋቋሚያ አዋጅ በሚደነግገው መሠረት የተመዘገበ እና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል።
ምእመናን እና ምእመናት በውቀታቸው፤ በገንዘባቸው ቦታና ጊዜ፤ ዘርና ጎሳ ሳይለያቸው ሁሉም በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ አካል ሆነው የእግዚአብሔርን ስም እየጠሩና እያመሰገኑ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ እና ሥርዓተ አምልኮ የሚፈጽሙበት በታ ነው።
መንፈሳዊ አገልግሎትን ለመስጠት በቅርቡ አዲስ ቦታ በመግዛት ህንጻ በመገንባት ላይ ይገኛል ። ቦታው በስፋት 14 ሄክታር ላይ የተቀመጠ ሲሆ በተፈጥሮ ውብና ማራኪ የሆነ ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚውል ነው ።
ቤተክርስቲያኑ ዘወትር ለምእመናን ክፍት ሲሆን በተጭማሪም የቅዱስ ገብርኤል እና የእናታችን የልደታ ለማርያምን ወርሃዊ በዓላት የጸሎተ ኪዳንና ሥርዓተ ቅዳሴ አገልግሎት ይሰጣል።
There are no upcoming events at this time.