“…አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል…” ማቴ 6፥33
- ተተኪው ትውልድ ሃይማኖቱን፤ባህሉን፤ ቋንቋውን እንዳይረሳ
- ማስተማር። በመንፈሳዊ ህይውት፣ በግብረ-ገብነት፣ በዘመናዊ እና በሳይንሳዊ መንገድ ተወዳዳሪና ተመራጭ እንዲሆኑ ማስቻል።
- አሜሪካዊነትን እና ኢትዮጵያዊነትን አጣጥመው፤ የተሟላ ስብዕና የተጎናጸፈ ዜጋ እንዲሆኑ መርዳት
- በሀይማኖታዊ ዕውቀታቸው እንዲጎለብቱና እንዲጠነክሩ ጥልቀት ያለዉ መንፈሳዊ፣ ተከታታይ ትምህርት በማስተማር
- የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ማስፋፋትና ማጠናከር።
- የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን ማደራጀት ማጠናከር።
- በኢትዮጵያ የሚገኙትን ገዳማትና አድባራት እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቶችን መርዳትና ማጠናከር።
- የቤተክርስቲያንን ዶግማ እና ቀኖና መጠበቅና ማስጠበቅ
- ምዕመናን ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው እንዲያውቁና በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር እንዲኖሩ ማድረግ
- ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚተላለፈንና የሚወጣውን ሃይማኖታዊ ውሳኔ መቀበና በተግባር መተርጐም።
- ልዩ ልዩ ምግባረ ሠናይ ድርጅቶችን ማቋቋም።
- በአካባቢው ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ጋር ሕብረት በፍጠር አገልግሎት መስጠት።